House of Restoration Church Ethiopia

House of Restoration Church Ethiopia Affiliated With Living Word International Church

24/08/2026

"ስነ ክርስቶስ" ከ ዶ/ር ግርማ በቀለ ጋር:: ሁላችሁም ተጋብዛችህል:: ለzoom ቁጥርና የበለጠ መረጃ ፓስተሩን ይመልከቱ::

23/08/2026
✨ የእሁድ ውብ የጌታ ቀን በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን! ✨ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን ልዩ የጸሎት፣ የአምልኮ እና የእግዚአብሔር ቃል ጊዜ ነበረን።በመድረኩ...
23/08/2026

✨ የእሁድ ውብ የጌታ ቀን በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን! ✨
ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን ልዩ የጸሎት፣ የአምልኮ እና የእግዚአብሔር ቃል ጊዜ ነበረን።
በመድረኩ መጋቢ እንግዳ ከዮሐንስ ወንጌል 10:10 በመነሳት "የተትረፈረፈ ሕይወት" በሚል ርዕስ ድንቅ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍሎናል።የተትረፈረፈ ሕይወት
1. በመንፈሳዊ ሕይወት በረከት፡ የልብ ሰላም፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ የጸሎትና የቅዱሳን ህብረት የተትረፈረፈ ሕይወት መሠረት እንደሆኑ፤
2. ምድራዊ በረከትና እረፍት፡ ጌታ ኢየሱስ ነፃ ካወጣን በኋላ ምስኪኑን ከጉድፍ የሚያነሳ፣ በምድራዊ ሕይወታችንም እረፍትና ሙሉ በረከትን የሚሰጥ አምላክ እንደሆነ ተምረናል።
በተጨማሪም ዘማሪት እየሩሳሌም አርጋው ከመዘምራን ቡድን ጋር በመሆን በድንቅ አምልኮ አገልግላለች። ጉባኤው በትንቢታዊ መንፈስና በእግዚአብሔር ክብር የተሞላ ልዩ ጊዜ ነበር!
«እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።» ዮሐንስ 10:10
#መታደስቤት #የተትረፈረፈሕይወት #የእሁድአምልኮ #እግዚአብሔርመልካምነው #አምልኮ

23/08/2026
✨ የአምልኮ፣ የጸሎትና የቃል ጊዜ! ✨“ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤” ኤፌ 5፥10የጌታ ቅዱሳንና ወዳጆች በሙሉ! በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን በተዘጋ...
22/08/2026

✨ የአምልኮ፣ የጸሎትና የቃል ጊዜ! ✨
“ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤” ኤፌ 5፥10
የጌታ ቅዱሳንና ወዳጆች በሙሉ! በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን በተዘጋጀው ልዩ የአምልኮ፣ የጸሎት እና የእግዚአብሔር ቃል ጊዜ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።
📌 የፕሮግራም መረጃ፦
📅 ቀን፦ እሁድ ጥቅምት 17
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን (ሲኤምሲ የተባበሩት ማደያ አጠገብ፣ እጅጋየሁ ዲባባ ህንፃ ቤዝመንት)
👉 ይህንን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ የዚህ ታላቅ በረከት ተካፋይ ያድርጓቸው!

📢 ልዩ የፈውስ፣ የነጻ መውጣት እና የአምልኮ ጥሪ!«ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከጥፋታቸውም አዳናቸው ።» መዝሙር 107፥20በህመም፣ በጭንቀትና በተለያዩ የህይወት እሰራቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች፤...
20/08/2026

📢 ልዩ የፈውስ፣ የነጻ መውጣት እና የአምልኮ ጥሪ!
«ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከጥፋታቸውም አዳናቸው ።» መዝሙር 107፥20
በህመም፣ በጭንቀትና በተለያዩ የህይወት እሰራቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች፤ የእግዚአብሔር የፈውስ እጅ በሚገለጥበት በዚህ ድንቅ ፕሮግራም ላይ እንድትታደሙ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።
🗓 ቀን፦ አርብ ነሐሴ 15
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በመታደስ ቤተክርስቲያን (ሲኤምሲ የተባበሩት ፀሐይ ሪል እስቴት ፊት ለፊት - የእጅጋየሁ ዲባባ ሕንፃ ቤዝመንት)
📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0948242526
👉 ሼር (Share) በማድረግ ለሌሎችም የምስራቹን ያድርሱ!
#አምልኮ

🔥 ታላቅ የመሻገር ኮንፈረንስ! 🔥"ወደ 2019 ዓ.ም አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ክብር እና ድንቅ የሽግግር ጊዜ "ነጻ የሚያወጣ፣ ሕይወትን የሚለውጥ እና ወደ ተነገረልን ተስፋ የሚያሸግር የእግዚአ...
18/08/2026

🔥 ታላቅ የመሻገር ኮንፈረንስ! 🔥
"ወደ 2019 ዓ.ም አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ክብር እና ድንቅ የሽግግር ጊዜ "
ነጻ የሚያወጣ፣ ሕይወትን የሚለውጥ እና ወደ ተነገረልን ተስፋ የሚያሸግር የእግዚአብሔር ቃልና መንፈሳዊ ድግስ ተዘጋጅቷል!
✨ በአገልግሎቱ ጊዜ:
* የእግዚአብሔር ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሰበካል።
* እግዚአብሔር በእውነት እና በመንፈስ ይመለካል።
* በልዩ ልዩ ችግር ውስጥ ላሉ፣ ለበሽተኞች እና እስራት ላለባቸው ሁሉ በኃይል ይጸለያል!
🗓 ቀን: ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 1 (አርብ እና እሁድ ብቻ)
⏰ ሰዓት: ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ: በመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን
👉 በእምነት ይምጡ፤ አዲሱን ዓመት 2019 ዓ.ምን በትንቢታዊ ቃል እና በእግዚአብሔር ኃይል እንቀበል!

18/08/2026
የእግዚአብሔርን ፊት ያየንበት እና የሰማይ መስከት የተከፈተበት እሁድ! 🙏✨​እጅግ  በእግዚአብሔር መገኘት በተሞላው የመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን የእሁድ (ሰኔ 10) አምልኮ ቆይታችን እግዚአብ...
17/08/2026

የእግዚአብሔርን ፊት ያየንበት እና የሰማይ መስከት የተከፈተበት እሁድ! 🙏✨
​እጅግ በእግዚአብሔር መገኘት በተሞላው የመታደስ ቤት ቤተክርስቲያን የእሁድ (ሰኔ 10) አምልኮ ቆይታችን እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ሠርቷል።
​በዚህ ልዩ የዝማሬና የቃል ጊዜ፡
​ፓስተር ፋሲል አንድአድርጌ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የህይወት ቃል መልእክት አጋርተውናል።
​ዘማሪ ዳንኤል ነበዲዳ ከቤተክርስቲያናችን አምልኮ መሪዎች ጋር በመሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ወደር በሌለው አምልኮ ጌታን ከፍ አድርገናል!
​📖 የዕለቱ የቃል ርዕስ፦ "ወንጌል"
1. ወንጌል የምስራች ነው!
"መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥..." (1ኛ ቆሮንጦስ 15፥1-4)
​ወንጌል የፍርሃትና የፍርድ ዜና ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተሰጠን የታላቅ ፍቅር እና የነፃ ስጦታ የምሥራች ነው።
2. ​ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ
እንዲሁም ሮሜ 5፥19 "በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።" መነሻ በማድረግ፤ የውርስ ኃጢአትና የሕግ ኃጢአት ምን እንደሆኑ ተመልክተናል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በደሙ ዋጋ ከዚህ ሁሉ ነፃ እንዳወጣን ኃይለኛና ነፃ የሚያወጣ ቃል ተካፍለናል!
​እኛ በኃጢአት ሙታንና ከእግዚአብሔር የተለያየን ነበርን፤ ነገር ግን ፍቅሩ ያስገደደው ኢየሱስ በእኛ ፋንታ በመስቀል ላይ ሞትን በመቅመስ ቤዛችን ሆነ።
3. ​ስለ ሙታንና ስለ ኃጢአት የተከፈለው ዋጋ
​በዕለቱ እንደተማርነው፤ በታዘዘው አንድ ሰው (በክርስቶስ) መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን እንዲሆኑ፣ የኃጢአት ኃይልና ሥርዓት በመስቀል ላይ ተሽሯል።
​ይህን ድንቅ ጊዜ ለሰጠን ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን።
​ #መታደስቤትቤተክርስቲያን #አምልኮ #ወንጌል #ፓስተርፋሲልአንድአድርጌ #ዘማሪዳንኤልነበዲዳ #እሁድአምልኮ

16/08/2026

What if the burden you’ve been carrying was never meant to be yours...

Address

CMC Round About Near Yetebaberut Gas Station
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911567590

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when House of Restoration Church Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to House of Restoration Church Ethiopia:

Shortcuts

Share

Category