25/12/2021
መጽሐፍ ቅዱስን የተፃፈው በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን ለመፃፍም ከ1600 ዓመታት በላይ
ፈጅቷል፡፡ የተፃፈውም 40 በሚደርሱ ቢያንስ በ11 የሥራ መስኮች ላይ በተሠማሩ (ከንጉስ እስከ ግብርና
ባለሙያዎች) ቢያንስ በ3 አህጉሮች በሚገኙ 11 አገሮች ውስጥ ባሉ ሠዎች ነው፡፡
በዓለም ላይ ያሉ
መጽሐፍት የተለያዩ ጥራዞች ሲኖራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ጥራዝ የሌለው ብቸኛው መጽሐፍ ነው፡፡
መፅሐፉ 66 ሙሉ በሙሉ የተቀናጁ እና የማይጣረሱ ምእራፎች አሉት፡፡ መጽሐፉን የፃፉት ሠዎች
ቢሆኑም የተፃፈው ግን በመገለጥ፤ በሚያበረታታውና በሚመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡
በ2ኛው ጢሞቴዎስ 3፤16 እነደተነገረው ቅዱሣት መጽሐፍት ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ባለበት
ሰው የተጻፉ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባት የሚለውን የግሪኩ ቃል እስትንፋስ ሲለው ይህም
የእግዚአብሔር ትንፋሽን ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በሠው ፀሐፊዎች
አማካይነት እስትንፋሱን ያሳቀመጠበት መጽሐፍ ነው፡፡
እኒዚህ ከሶስትና ከአራት ጥቅሶች በፊት በመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በራእይ መጽሐፍ
ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚሠማውን ሁል አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህች
የትንቢት ቃል ላይ አንዳች ቢጨምር፤ እግዚአበሔር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተፃፉትን መቅሰፍቶች
ይጨምርበታል፤ ማንም በዚህች የትንቢት መጽሐፍ ከተፃፈው ቃል እንዳች ቢያጎድል፤ እግዚአብሔር
በዚህ መጽሐፍ ከተፃፉት ከህይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እድሉን ያጎድልበታል (ራእይ 22፤18-
19)፡፡
ዮሐንስ በመፅሐፉ ውሰጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል የጠቀሰው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የብሉይ
ኪዳን ነብያት እንዲሁም የአዲስ ኪዳን መሰረታዊ አስተምህሮቶች እና ነቢያት ያስጠነቀቁት መጽሐፍ
ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የዮሐንስ ማስጠንቀቂያ የሚያሳየው የነገስታት ንጉስ
የጌቶችም ጌታ ዳግም ምፅአት ድረስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተገለጠበት 66 የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎች መኖራቸውን ነው፡፡
ብዙ ውጊያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተነስተዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ህግ አስከባሪ ነን ባዮች ስህተት
ለመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበውት አማኞች ሆነው ቀርተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክን
በሚያወሳባቸው ጉዳዮች የታሪክ ባለሙያዎች እና አርኪዮሎጂስቶች በሚያስገርም ሁኔታ ትክክል እንደሆነ
መስክረውለታል፡፡ ሣይንስን በተመለከተም በሚያነሳቸው ጉዳዮች ትክክል እንደሆነ ተምኖበታል (ስለ
ዓለም አፈጣጠር እና ስለ ሰው ልጆች አመጣጥ እንኳን ሣይቀር)፡፡ እሰኪ ይህ ሣይንቲሰት ከብዙ ድካም
በኋላ የመሰከረውን እንመልከት፡፡
በአርኪኦሎጂ ቁፋሮ ወቅት በተመሳሳይ የጊዜ ክፍተት ውስጥ በአበባነት ጊዜያቸው በተለያየዩ ቦታዎች
የሞቱትን የእፅዋት ቅሪተ አካል ተመሳሳይነት በድንገት አገኘን፡፡ በእነርሱ ላይ ልዩነት በፍጹም
አይታይም፡፡ ይህ ሁሉ ከዘገምተኛው የህይወት ለውጥ አስተሳሰብ የሚቃረን ድንቁርና ….. ሁሉም
ምርምሮቼ ወደ ሚያስገርም ተቃራኒ ውጤት…..በዚህ ምክንያት የዘገምተኛ ለውጥ አስተሳሰብ ሙሉ
በሙሉ ውድቅ ሆነ…. ለሥነ ህይወት ትምህርት ምርምር አስቸጋሪው እንቅፋት፡፡ በዚህ ምክንያት
የዘገምተኛ ትምህርት አስተሳሰብን በቤተ ሙከራ ለማሳየት የታሰበ የ40 ዓመታት ልፋቴ ሙሉ በሙሉ
ከንቱ ቀረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የታመነ ነው፡፡
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሠማይንና ምድርን ፈጠረ (ዘፍጥረት
1፤1)፡፡ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሠውን ከምድር አፈር ሰርቶት እስትንፋሱን እፍ አለበት
( ዘፍጥረት 2፤7)፡፡
የትኛውም መጽሐፍ ፍቅርን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አይገልፅም፡፡ መፅሐፉም ባልንጀራህን
እንደራስህ ውደድ (ዘሌዋውያን 19፤18፤ ማቴዎስ 22፤39) እንዲሁም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤
ለሚሳድዷችሁም ፀልዩ (ማቴዎስ 5፤44) ይላል፡፡ ይህ ፍቅር የጋብቻን ውበትና በረከት ያሳያል፤
ይህንንም የተከበረውን አስገራሚ የሰዎች ግንኙነት የሚያሠጋን ማንኛውንም ነገር ይኮንናል፡፡ ይህ ፍቅር
ዓለምን እንደ ሱናሚ ማዕበል እያጥለቀለቀ ለሴቶች፤ ለወላጆች፤ ለአዛውንቶች፤ ለህፃናት፤ ዳግም
በክረስቶስ ላልተወለዱ፤ ለድሆች፤ ለአካል ጉዳተኞች እና ለመፃተኞች ክብርን ያጎናፅፋል፡፡ በእርግጥ ይህ
የቃሉ ፍቅር የሰው ልጆችን ከሚወደው ፍላጎቱም እነርሱን ማዳንና በማናኛውም በኩል መባረክ ከሆነው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡