Lg-Koica Hope TVET college students የሰአሊተምሕረት ጊቢ ጉባኤ

  • Home
  • Lg-Koica Hope TVET college students የሰአሊተምሕረት ጊቢ ጉባኤ

Lg-Koica Hope TVET college students የሰአሊተምሕረት ጊቢ ጉባኤ ስለሁሉም መልካም ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን

100% የተጠናቀቀ ቤት ፈልገው አጥተዋል? እንግዳውስ እኛ ጋር ይምጡ። የተናጠል ካርታ የተዘጋጀላቸው አፓርትመንት ቤቶችን ቫሞስ ሪል እስቴት በጋርመንት አካባቢ ስራውን አጠናቆ እየጠበቃችሁ ይ...
02/05/2026

100% የተጠናቀቀ ቤት ፈልገው አጥተዋል?
እንግዳውስ እኛ ጋር ይምጡ።
የተናጠል ካርታ የተዘጋጀላቸው አፓርትመንት ቤቶችን ቫሞስ ሪል እስቴት በጋርመንት አካባቢ ስራውን አጠናቆ እየጠበቃችሁ ይገኛል።
:-
* ቤቶቹ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቁ መሆናቸው
* ግንባታ የተከናወነባቸው ማቴሪያሎች አውሮፓውያን ስታንዳርድ መሆናቸው
* 50% የባንክ ብድር የተዘጋጀ መሆኑ
* እያንዳንዳቸው የተናጠል ካርታ የተዘጋጀላቸው
* የከርሰ ምድር ውሃ ያለው እና ዘመናዊ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ያለው
* እያንዳንዱ ቤት እራሱን የቻለ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ያለው
* በአንድ ፍሎር 6 አባወራዎች ብቻ የሚኖሩበት
* ለ6 ቤቶች 2 መወጣጫ ሊፍቶች (Elevators) ያሉት
* የአደጋ ጊዜ መውጫ የተዘጋጀለት
* 24 ሰዓት ዝግጁ የሆነ ባክአፕ ጀነሬተር ያለው
* ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ የተዘጋጀለት
* የሰራተኛ ክፍል ያላቸው
* ከ126 እስከ 227 ካሬ
* በካሬ 95,000 ብር
* የእንግዳ መቀበያ (Reception area) ያለው
* ሙሉውን መክፈል ካልቻሉ 50% ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን በአንድ አመት መክፈል ይችላሉ።
ውስን ቤቶች ስለቀሩን እንዳያመልጥዎት ይፍጠኑ።
ለበለጠ መረጃ
ያነጋግሩን 👇
📩 [email protected] | 📞 +251941259051/+251712271245

https://www.facebook.com/profile.php?id=61588863577228

 ...እንኳን_አደረሳችሁ!ሞትን በሞቱ የሻረ፣ በመቃብር ላሉት ህይወትን የሰጠ... ክርስቶስ ተነስቷል!እርሱ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ በመቃብር አድሮ፣ በሶስተኛው ቀንም በታላቅ ሃይልና...
12/04/2026

...እንኳን_አደረሳችሁ!
ሞትን በሞቱ የሻረ፣ በመቃብር ላሉት ህይወትን የሰጠ... ክርስቶስ ተነስቷል!
እርሱ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ በመቃብር አድሮ፣ በሶስተኛው ቀንም በታላቅ ሃይልና ስልጣን ተነስቷል። የትንሳኤው ብርሃን በእያንዳንዳችን ህይወት ላይ ይብራ። ጥላቻ በቅንነት፣ ጨለማ በብርሃን ይሸነፍ።
ይህ በዓል ለሀገራችን ሰላም፣ ለህዝባችን ፍቅር እና መተሳሰብን ይዞልን ይምጣ። እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
#ትንሳኤ #ፋሲካ #ክርስቶስተነስቷል #ስቅለት #ኢትዮጵያ "

 #ሆሳዕናየሆሳዕና ክብረ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እጅግ በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ታላቅ በዓል ነው። ይህ በዓል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ እየ...
05/04/2026

#ሆሳዕና
የሆሳዕና ክብረ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እጅግ በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ታላቅ በዓል ነው። ይህ በዓል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ እየሩሳሌም ሲገባ፣ ሕዝቡ ‘ሆሳዕና በአርያም’ (በአርያም መድኃኒት) እያለ ዘንባባ እና ልብሶችን በመጎዝጎዝ በደስታ የተቀበለበትን ታሪካዊ ክስተት ለማስታወስ የሚከበር ነው። በዓሉ የሚከበረው ከትንሣኤ (ፋሲካ) አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ባለው እሁድ ነው።
በኢትዮጵያ የሆሳዕና በዓል አከባበር ዋና ዋና መገለጫዎች የሚከተሉት ናቸው፡
የዘንባባ ዝንጣፊ (ዘንባባ): ምዕመናን ከቤተክርስቲያን የተባረከ ዘንባባ ይቀበላሉ። ይህን ዘንባባ በግንባራቸው ላይ፣ በቀለበት፣ ወይም በመስቀል ቅርጽ በመጠቅለል፣ እንዲሁም በእጃቸው በመያዝ ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።
የሕፃናት ዝማሬ: ‘ሆሳዕና በአርያም’ እያሉ ሕፃናት በደስታ ይዘምራሉ፣ ይህም ኢየሱስን የተቀበሉትን የኢየሩሳሌም ሕፃናትን ያስታውሳል።
የካህናት ዑደት: የቤተክርስቲያን አባቶች በቀለማት ያሸበረቁ አልባሳትን በመልበስ፣ ጸናጽልን በመምታት፣ ከበሮን በመደለቅ እና የሰሌን (ዘንባባ) መስቀሎችንና በትረ መስቀሎችን በመያዝ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ዑደት ያደርጋሉ።
!
#ሆሳዕና #ለመድኃኔዓለም

እንኳን  #ለመድኃኒዓለም በዓል በሰላም አደረሳችሁ!ዛሬ የዓለም መድኀኒት የምድር እና የሰማይ እንዲሁም የፍጥረት ሁሉ ገዢ የመድኃኒዓለም በዓል ነው። ይህ ቀን የክርስቶስን ስቅለት፣ ሞት፣ እና...
05/04/2026

እንኳን #ለመድኃኒዓለም በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዛሬ የዓለም መድኀኒት የምድር እና የሰማይ እንዲሁም የፍጥረት ሁሉ ገዢ የመድኃኒዓለም በዓል ነው። ይህ ቀን የክርስቶስን ስቅለት፣ ሞት፣ እና ትንሣኤ በማሰብ፣ የመዳኛ ተስፋችንን የምናድስበት ነው።
በዓሉን የምታከብሩ ሁሉ፣ ከቤተሰቦቻችሁ እና ከወዳጆቻችሁ ጋር በሰላም፣ በፍቅር እና በደስታ እንድታከብሩ እመኛለሁ። የመድኃኒዓለም በዓል በቤታችሁ ሰላምን፣ በልባችሁ ፍቅርን፣ እና በህይወታችሁ በረከትን ያምጣላችሁ።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

ሆሳዕና በአርያም! - የሰላም ንጉሥ መግቢያ​"በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ የእስራኤል ንጉሥ።" (ዮሐ. 12፡13)​ዛሬ የዓብይ ጾም ማጠቃለያ እና የሕማማት ሳምንት መግቢያ የሆነው ታላቁ...
05/04/2026

ሆሳዕና በአርያም! - የሰላም ንጉሥ መግቢያ
​"በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ የእስራኤል ንጉሥ።" (ዮሐ. 12፡13)
​ዛሬ የዓብይ ጾም ማጠቃለያ እና የሕማማት ሳምንት መግቢያ የሆነው ታላቁ በዓል ሆሳዕና ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትሕትና በአህያ ውርንጭላ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፣ ሕዝቡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው "ሆሳዕና በአርያም" እያሉ ተቀብለውታል።
​ሆሳዕና ማለት "አሁን አድን" ማለት ነው።
​ዘንባባው የድል ምልክት ነው።
​እኛም ዛሬ የልባችንን በር ከፍተን፣ ትዕቢታችንን ጥለን፣ በትሕትና ለሰላም ንጉሥ ለኢየሱስ ክርስቶስ የምስጋናና የ"አድነን" መዝሙር የምናቀርብበት ቀን ይሁንልን።
​🌿 እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሰን! 🌿

29/03/2026

ኒቆዲሞስ - ዳግም የመወለድ ምስጢር
​"ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም።" (ዮሐ. 3፡3)
​በዓብይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ቤተክርስቲያናችን ስለ ኒቆዲሞስ ታስተምረናለች። ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምስጢር ጠየቀ። ጌታችንም "ዳግም መወለድ" እንደሚገባው ነገረው።
​ይህ ሳምንት ለሁላችንም እንደ ኒቆዲሞስ ዳግም የመወለድን ትርጉም የምንረዳበት፣ በጸሎትና በንስሐ ወደ አምላካችን የምንቀርብበት ይሁን።
​መልካም የጾም ሳምንት!

28/03/2026

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
​"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ልናገርህም ይህችንም የምስራች ልነግርህ ተልኬ ነበር።" (ሉቃስ 1፡19)
​ዛሬ የአዋጅ ነጋሪው፣ የምስራች ሰባኪውና የመዳን አበሳሪው የታላቁ ሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል በዓል ነው።
​ቅዱስ ገብርኤል ለቅድስት ድንግል ማርያም የጌታን መወለድ አበሰረ።
​ለዘካርያስ የዮሐንስን መወለድ ነገረው።
​በፈተናና በጭንቅ ጊዜ ረዳትና ታዳጊ ነው።
​​"ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! በጥሪህ ምስራች እንደነገርከን፣ ዛሬም በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ጨለማ አስወግደህ የመዳንን ብርሃን አሳየን። ስለ እኛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር ለምን።"
​አሜን።
ይህ በዓል ለሁላችንም የመልካም ዜና፣ የሰላም እና የፈውስ በዓል ይሁንልን። የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
​🕊️ እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሰን! 🕊️

  ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው። #እንኳን ለቅድስት ኪዳነ_ምህረት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።  የቃል ኪዳኗ በረከት አይለየን። አሜን አሜን አሜን!!!
25/03/2026

ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው።
#እንኳን ለቅድስት ኪዳነ_ምህረት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የቃል ኪዳኗ በረከት አይለየን። አሜን አሜን አሜን!!!

Address

Bole, Gerji

1000

Telephone

+251941259051

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lg-Koica Hope TVET college students የሰአሊተምሕረት ጊቢ ጉባኤ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship?

Share