Gospel Servant Biruk Deme Alemu

Gospel Servant Biruk Deme Alemu “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።?

23/10/2021
Follow & Like Pages
10/10/2021

Follow & Like Pages

“የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።”  — ዕንባቆም 3፥7
30/06/2021

“የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።”
— ዕንባቆም 3፥7

ሐዋርያው ይዲዲያ ምድራችን አንተ ላይ ባለው ቅባት ትበለፅጋለች ለምልምልን እንወድሀለን።
24/05/2021

ሐዋርያው ይዲዲያ ምድራችን አንተ ላይ ባለው ቅባት ትበለፅጋለች ለምልምልን እንወድሀለን።

22/04/2021

“ክፉው ነገር አይደርስብንም፥ አያገኘንምም የሚሉ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።”
— አሞጽ 9፥10

Date: 21 Apr 2021Subject: ንገሩት ለዚያ ሰውሁሉም ሳይረዱህ አትችልም ሲሉህመንገድህን ይዘህስትሔድ ተጉዘህብቻህን ስትሮጥለሀገርህ ለውጥሳይቆሙ ከጎንህአለንልህ ሲሉህአንድነትን ጠል...
21/04/2021

Date: 21 Apr 2021
Subject: ንገሩት ለዚያ ሰው

ሁሉም ሳይረዱህ
አትችልም ሲሉህ
መንገድህን ይዘህ
ስትሔድ ተጉዘህ
ብቻህን ስትሮጥ
ለሀገርህ ለውጥ
ሳይቆሙ ከጎንህ
አለንልህ ሲሉህ
አንድነትን ጠልተው
ተንኮልን ሸርበው
ቀን እየጠበቁ
ከስርህ ሳይርቁ
በጥርሳቸው ስቀው
በእጅ አጨብጭበው
ሲያስመስሉ ኖረው
ስትነቃ ፈርጥጠው
ቦታ እየቀየሩ
ፈልገው እሹሩሩ
ብቻህን ስታዝል
ሁሉም ሲንጠለጠል
ማን ተረዳህና ዝም ማለትህን
ከሰላም በስተቀር ሌላ መጥላትህን
እራሱ ተኩሶ እራሱ ይጮሀል
እሱ በገደለው ባንተ ይሳበባል
ወንድሙን የሚገል ወንድም የተባለው
አንተን ለመቃወም ቤት የሚያቃጥለው
ሊያውም በዚህ ዘመን እውቀት ባልጠፋበት
እንዲያስተውል ብለህ ቡዙ የታገልክለት
ስደክም ብቻህን
ትተኸው ክብርህን
ዝቅ በማለትህ
ኩራት ለሀገርህ
ስታመጣ ለፍተህ
በብዙ ተናጥቀህ
ተቀምጦ ሳይሰራ
ጥላቻን የሚዘራ
ልትቀይር ታሪክን
አሮጌው ትውልድን
ስትጥር ያለ ዕረፍት
ልታስቀር ድህነት
ስትሰራ ከልብህ
ያለ ምክንያት ጠሉህ
ሲጠግብ ሆዳቸው
ወፍሮ ስጋቸው
ጭንቅላት ኖሯቸው
ማሰብ አቃታቸው
አንተን ከመረዳት
አሳልፎ መስጠት
በሰው ነፍስ ቀልደው
ክህደት ጀምረው
ያልቃሉ ራሳቸው
ጥቂት ነው ቀናቸው
ንገሩት ለዚያ ሰው
ልማት ለሚወደው
ቀጥል የኔ መሪ
ሰላምን አብሳሪ
ሁሉም ካንተ ቢርቅ
ስላልቻለ መስረቅ
እኔ ግን ከጎንህ
አለሁ ልደግፍህ
ሐሳብህ መልካም ነው
ኢትዮጲያን ያሰብከው
የዘመኑ ሙሴ
ወዳሀለች ነፍሴ
ፈጣሪ ይጠብቅህ
በመንገድህ ይምራህ
አትፍራ ወጀቡን
አበርታው ልብህን
እውነት ብትከሳ ብትመነምንም
ተባብረው ቀብረዋት ሞታለች ቢሏትም
መቃብር ሳይዛት ትመጣለች ወታ
ትንሳኤ ነውና ህይወት የእውነታ
የሚወድህና የሚረዳህ ትውልድ
ከፊትህ ስላለ አትቁም ከመንገድ
ሌላ ቃል የለኝም አለኝ ግን አልፅፍም
አንተን በብዕሬ ጠቅሼ አልጨርስም
ባለህበት ሁሉ ጤናህን ተመኘሁ
ዶ/ር አብይ አንተን ሁሌም እወድሀለው

ገጣሚና ፀሐፊ
ብሩክ፡ ደሜ Dat 13-08-2013E.C

17/04/2021

“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና .....

Address

Grace Redemption
Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gospel Servant Biruk Deme Alemu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category