ማኅበረ ጽድቅ

  • Home
  • ማኅበረ ጽድቅ

ማኅበረ ጽድቅ ፍፁምነት የሚገኘው ለሰው በመኖር ውስጥ ነው

እንዴት ናችሁ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወዳጆች እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ኀዳር 25 እሁድ ወደ ቀጸባ ማርያም እንዲሁም ደብረሊባኖስ ደርሶ መልስ ተሳልመንና ተባርከን እንመጣለን ።ሁላ...
10/11/2022

እንዴት ናችሁ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወዳጆች እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ኀዳር 25 እሁድ ወደ ቀጸባ ማርያም እንዲሁም ደብረሊባኖስ ደርሶ መልስ ተሳልመንና ተባርከን እንመጣለን ።ሁላችሁም በግሩፖችና በየግል ሶሻል ሚዲያዎቻችሁ ሼር አርጉት ገቢው ሙሉ ለሙሉ ለገጠር ቤተክርስቲያን የሚውል ነው።።
እንዳይሞላ ትኬት ቀድመው ያሲዙ
እስራኤል ደመቀ ነጋሽ 1000107229594

፳፩-፳፭እንኳን አደረሳችሁ ዛሬ እመቤታችን ከአምላካችን ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር የተሰደደችበት ዕለት ነው  የሕይወት እንጀራና መጠጥ ይዛ ተራበች ተጠማች አቤቱ ስላንቺ መፃፍ ምነኛ ጭንቅ ...
01/06/2022

፳፩-፳፭እንኳን አደረሳችሁ ዛሬ እመቤታችን ከአምላካችን ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር የተሰደደችበት ዕለት ነው የሕይወት እንጀራና መጠጥ ይዛ ተራበች ተጠማች አቤቱ ስላንቺ መፃፍ ምነኛ ጭንቅ ነው ባለኝ አቅም አመሰግንሻለሁ ፍቅርሽ በገባኝ መጠን እወድሻለው ግን ደግሞ የፍቅር እናት ነሽና ሀጢያት ባሸፈተው ልቦናዬ ላይ ፍቅርሽን ይበልጥ አሳድሪበት ንፁህም ይሆናል ትህትናንም ይላበስልኛል ያኔ መልካሙን ቅኔ እቀኝልሻለው •እመቤታችን ሆይ ምነኛ ውብ ነሽ•💙
፳፬ ለአባታችን ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ አባ ምግባረ ቢሶቹ በስምህ ተሰባስበን እንጠራሀለን ፀሎታችን ራቁቷን እንዳትገባ አንተን መልበስ ተስፋ ሁናት እመብርሃን ትጠብቀን አባታችን ተክለሃይማኖት ረድኤቱ አይለየን

እንኳን ለግንቦት ፲፪ የአባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም ዓመታዊ በዐል በሰላም አደረሳችሁ ❤  ዘተሴሬ በደም ፡ አመ እግርከ ተሰብረ በብዝኃ ቀዊም ፡ ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስ...
20/05/2022

እንኳን ለግንቦት ፲፪ የአባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም ዓመታዊ በዐል በሰላም አደረሳችሁ ❤
ዘተሴሬ በደም ፡ አመ እግርከ ተሰብረ በብዝኃ ቀዊም ፡ ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ ኢዮብ ዘትዕግስትከ ፍፁም ፤ ለያቂቅከ እለ ኲሉ ዓለም ፡ ከመ ባረኮሙ ኖኅ ለያፌት ወሲም።❤️

🙏ተክለሃይማኖት ሆይ በቁመት ብዛት እግርህ በመሰበሩ በደም ለተነከረ ሰኮናህ ሰላም እላለሁ
ቅዱሱ አባት ሆይ ትዕግስትህ ፍጹም እንደ እዮብ ትዕግሥት ነው እኮን አባት ሆይ ኖኅ ልጆቹ ሴምንና ያፌትን እንደባረካቸው አንተም በዓለሙ ሁሉ ያሉ ልጆችህን ደቀ መዛሙርትህን ባርካቸው።

የጅማሬም የፍፃሜም ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን ታናሽነታችንን አይቶ ምንም ምግባር ባይኖረን በሀጢያት ውስጥ ብንሆን ሞገስ ሰጥቶን በእናንተ በወንድሞች ገንዘብ ጉልበት ጸሎት ነዳያንን በፈቀደ...
02/05/2022

የጅማሬም የፍፃሜም ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን ታናሽነታችንን አይቶ ምንም ምግባር ባይኖረን በሀጢያት ውስጥ ብንሆን ሞገስ ሰጥቶን በእናንተ በወንድሞች ገንዘብ ጉልበት ጸሎት ነዳያንን በፈቀደልን መልኩ ጎብኝቶናል እርሱ አተረፍርፎ ይስጣችሁ እመብርሐን ትጎብኛችሁ የጻድቁ አባታችን በረከት ለሁላችን ይሁን አሜን💙

ጌታችን፧ ተርቤ አላበላችሁኝም ታርዤ አላለበሳችሁኝም፥ ይለናል  የት አግኝተን አላበላንህም አላለበስንህም እንንለው ይሆናል እነሆም በደጃችሁ ነዳይ ሆኜ እገኝ ነበር ብሎ ይመልሳል፤ እኛስ መልሳ...
14/04/2022

ጌታችን፧ ተርቤ አላበላችሁኝም ታርዤ አላለበሳችሁኝም፥ ይለናል
የት አግኝተን አላበላንህም አላለበስንህም እንንለው ይሆናል እነሆም በደጃችሁ ነዳይ ሆኜ እገኝ ነበር ብሎ ይመልሳል፤
እኛስ መልሳችን ምን ይሆን???

እንደ አምላክ ፈቃድ እንደ አቡነ ምልጃ ተሳልመን መጥተናል ከእመቤቴ ደጇ💙
11/04/2022

እንደ አምላክ ፈቃድ እንደ አቡነ ምልጃ
ተሳልመን መጥተናል ከእመቤቴ ደጇ💙

💒ተወዳጅ ቤተሰቦች የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 02 ዕለተ ኒቆዲሞስን በእናታችን ቤት እናሳልፍ ትላለች ማኀበራችን ጊዜው አጭር ነው ፈጥነው ትኬቱን ይውሰዱ🚎
04/04/2022

💒ተወዳጅ ቤተሰቦች የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 02 ዕለተ ኒቆዲሞስን በእናታችን ቤት እናሳልፍ ትላለች ማኀበራችን ጊዜው አጭር ነው ፈጥነው ትኬቱን ይውሰዱ🚎

ተክለሃይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀነስከው ፅንሰትህና በታህሳስ 24 ለተወለድከው መወለድህ ሰላም እላለው እኔን አገልጋይህን ጥለህ አትጣለኝ አንዲቷ ጸሎትህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀጢያቶቼ...
01/04/2022

ተክለሃይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀነስከው ፅንሰትህና በታህሳስ 24 ለተወለድከው መወለድህ ሰላም እላለው እኔን አገልጋይህን ጥለህ አትጣለኝ አንዲቷ ጸሎትህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀጢያቶቼን እንደጉም አብና እንደጢስ አትና ታጥፋቸው እንጂ
እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት ፅንሰት ዓመታዊና ለወላጆቻቸው እግዚእ ሀረያና ፀጋ ዘአብ ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሳችሁ

27/02/2022

፨ዛሬ ሽቱ መስበሪያ ቀን ነው፨
አካላቱ በጭቃ የተለወሰ ጠረኑም የከረፋ ሰው ምንም ፀአዳ ለብሶ ካባ ቢደርብ ሽቱም ቢቀባ አያምርበትም ምክኒያቱም ጭቃው ካማረው ልብስ ጋር መጥፎ ጠረኑም ከመልካም ሽቶው ጋር በህብረት ስለማይቀመጡ ፤ እና ለምን ይህን አልኩ? ነገ ትልቅ በረከት ያለው ደግስ ተጠርተናል ድግስ ውስጥ ለመግባት በጭቃ በተለወሰውና በመጥፎ የሀጢያት ጠረን የተሸፈነው ሰውነታችንን መታጠብና መልካም መአዛን መጎናፀፍ ያስፈልገዋል ፨ እና ምን እናርግ?
የጌታችን እግር በምኩራቡ እየጠበቀን ነው እግሮቹም ሽቶዎቻችንን ናፍቀዋል ሄደን እንባን ከፀፀት ደባልቀን እግሩን እንጠበው።
፨ጌታችን የት ሆኖ ይሆን የሚጠብቀን?
በንስሃ አባቶቻችን በኩል ቆቡን ለብሶ መስቀሉን ይዞ በቤተክርስቲያን ውስጥ ደጅ ደጁን እያየ መምጫችንን ናፍቋል ሄደን ራሳችንን ለአባቶቻችን እናሳይ እንናዘዝ የጌታችን እግር ላይ ሽቱ አፍስሰን እንደ ባለሽቱዋ ማርያም መልካም መአዛን ይዘን እንመለስ ።
የበረከት ያርግልን💙

26/04/2021

ሰላም እንዴት አደራችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ -- አሜን
# በጉዟችን ተከትሎ ሰላም አድርሶ የመለሰን የድንግል ማርያም ልጅ አምላከ ተክለሃይማኖት ምስጋና ይድረሰው።
*በጉዞው ላይ ተገኝተን መሰባሰባችንን እና ህብረታችንን በአንድ መቆማችንን ላሳየን ወንድም እህቶቼ ክብረት ይስጥልን።
# በተለያዩ ምክንያቶች መሔድ ፈልገው ያልተሳካላቸው ወንድም እህቶቼ አምላከ ተክለሃይማኖት ከቦታው ረድኤት በረከት ያሳትፍልን አሜን።
* ሁላችሁም በተፈጠሩብን አለመግባባቶች ይቅርታ እያልኩ አምላከ ተክልዬ ፈቅዶ ደግሞ ዳግም የተባረከ ቦታ ለመሳለም በረከቱን ለማግኘት ይርዳን
# ትናንት የነበርን አብረን ሰምተናል ያልነበረችሁ ጉዳዮ ይመለከታችኃል
- ለዳግማ ትንሳኤ ነድያንን ለመመገብ ፕሮግራም አድርገን ይዘናል ሁሉም አባላት አቅሙ የቻለውን እንዲሁ በዙሪያችን ቅርብ ያሉ ወንድም እህቶችን ከበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ የበረከት ስራ እንስራ ---
የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ አምላከ ተክለሃይማኖት ከሁላችንም ጋር ይሁን ሰላም ያሳደረን አምላክ ሰላም ያውልልኝ- -- አሜን ----- ወዳችኃለው።

📣📣📣ጉዞ ጉዞ ጉዞ🚎🚎🚎የተወዳጁ ማኀበራችን ማኀበረ ፅድቅ ሁለተኛው ጉዞ የፊታችን እሁድ የሆሳዕና እለት ሚያዝያ 17 ወደ እናታችን እመቤታችን ኣዳዲ ማርያም ይካሄዳል ያዘጋጀነው ቦታና ትኬት እ...
19/04/2021

📣📣📣ጉዞ ጉዞ ጉዞ🚎🚎🚎
የተወዳጁ ማኀበራችን ማኀበረ ፅድቅ ሁለተኛው ጉዞ የፊታችን እሁድ የሆሳዕና እለት ሚያዝያ 17 ወደ እናታችን እመቤታችን ኣዳዲ ማርያም ይካሄዳል ያዘጋጀነው ቦታና ትኬት እጅግ ጥቂት ነው ቀድመው ይቁረጡ ✝️

Address

Addis Ababa

Telephone

+251966244423

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ጽድቅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship?

Share