የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያንሚዲያ /EHBC.Media

  • Home
  • Ethiopia
  • Ababa
  • የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያንሚዲያ /EHBC.Media

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያንሚዲያ /EHBC.Media gives information about church activities

የኢትዮጵያ የህይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ ከሲንቄ ባንክ ከመጡ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ አብረው በሚሰሩበት ጉዳዮች ላይ  ውይይት አደረጉ፡፡በባንክ ኢንዱስት...
15/02/2024

የኢትዮጵያ የህይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ ከሲንቄ ባንክ ከመጡ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ አብረው በሚሰሩበት ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በፍጥነት እያደገና ተደራሽነቱነቱን እያስፋፋ ከመጣው ከሲንቄ ባንክ ጋር የተለያዩ የልማት ስራዎችን አብሮ ለመስራት የተነጋገሩ ሲሆን የባንኩ የስራ ኃላፊዎችም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለልማት ስራ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉና አብሮ ለመስራት በመወሰናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያን የቦርድ አባላት በአዲስ መልክ ተዋቅሮ ወደ አገልግሎት የገቡበት አንደኛ ዓመት እና በየሦስት ወሩ የሚካሄደውን መደበኛ ስብሰባ ዛሬ አዲስ አበባ በሚ...
12/10/2023

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያን የቦርድ አባላት በአዲስ መልክ ተዋቅሮ ወደ አገልግሎት የገቡበት አንደኛ ዓመት እና በየሦስት ወሩ የሚካሄደውን መደበኛ ስብሰባ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው በቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጽ/ቤት አካሂዷል ፡፡ በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ የተገኙ ሲሆን የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለው ለቦርድ አባላቱ ፀሎት አድርገው ስብሰባው በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል ፡፡

ዜና እረፍት !!በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለበርካታ አመታት በተለያዬ ከፍተኛ የአመራር ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትን የቄስ አለሙ ሼጣን ዜና እረፍት በታላቅ ሀዘን ሰም...
10/10/2023

ዜና እረፍት !!

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለበርካታ አመታት በተለያዬ ከፍተኛ የአመራር ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትን የቄስ አለሙ ሼጣን ዜና እረፍት በታላቅ ሀዘን ሰምተናል፡፡
ቄስ አለሙ ሼጣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት/ፕረዝደንትነት አገልግለዋል::
የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን በቄስ ዓለሙ ሼጣ ዜና እረፍት በጣም ያዘነች ሲሆን ለባለቤታቸው፣ ለልጆቻቸው፣ ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ምዕመናን ሁሉ እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጠን ጸሎታችን ነው።

"ርኆቦት"አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።                   ዘፍጥረት 26፡22የሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን  ዓመታዊ ኮንፍራንስ በመካሄድ ላይ ስለሆነ...
24/08/2023

"ርኆቦት"
አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።
ዘፍጥረት 26፡22
የሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ ኮንፍራንስ
በመካሄድ ላይ ስለሆነ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
ኑና የእግዚአብሔርን በረከት ተካፈሉ!

18/04/2023
ቀን ተቆረጠለት!!በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወዳጆቻችን እና አባሎቻችን ባቀረቡልን ጥያቄ  እኛም በገባነው ቃል መሰረት እግዚአብሔር ቢፈቅድ  የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከሁለት ቢሊየን ብር በለይ...
30/01/2023

ቀን ተቆረጠለት!!
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወዳጆቻችን እና አባሎቻችን ባቀረቡልን ጥያቄ እኛም በገባነው ቃል መሰረት እግዚአብሔር ቢፈቅድ የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከሁለት ቢሊየን ብር በለይ እንደሚፈጅ የሚገመተው የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የሕንፃ ግንባታ የፈንድሬዚንግ ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ እንደገለፁት የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በሀዋሳ ኃይሌ ሪዞርት የመጀመሪያው ዙር የፈንድሬዚንግ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ገልፀው በፕሮግራሙ ላይ የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ተወካዮች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የነጋዴዎች ሕብረት እንደሚገኙና ይህን ፕሮግራም የሚያስተባብሩ ኮምቴ አባላት መዋቀሩን ገልፀዋል፡፡

የሁለተኛው ዙር ፈንድሬዚንግ ፕሮግራም መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ እና በመቀጠልም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንደሚካሄድ የሕንፃ ግንባታ ኮምቴ አባላት አሳውቀዋል ፡፡
ለፕሮግራሙ መሳካትና ለሕንፃ ግንባታ ስራው በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ያላችሁ ወገኖች በሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች ድጋፋችሁ አይለየን በማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ ጥሪያቸውን አሰተላልፈዋል፡፡
1ኛ በፀሎት
2ኛ በፀሎት
3ኛ በፀሎት
እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ!!

Address

Addis Ababa
Ababa
62273

Telephone

+251911623508

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያንሚዲያ /EHBC.Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሀን ቤተ ክርስቲያንሚዲያ /EHBC.Media:

Shortcuts

Share

Category