21/11/2018
እንኳን ለእናታችን ጽዮን ማርያም ታላቅ አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን አደረሳቹ
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ ረድኤት በረከቷ ፍቅሯ ከመላው
ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን፡፡
ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል» መዝ.86-5; እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና” መዝ. 132፡13 ጽዮን ማለት አንባ መጠጊያ ማለት ነው፡፡ ታቦተ ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትሆን፣ በውስጡዋ የያዘችው የሕጉ ጽላት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቷ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቷ የጌታን እናት ንጽሕናን የሚያመለክት ሲሆን በውጪም በውስጧም በጥሩ ወርቅ መለበጡዋ የቅድስናዋና ድንግል በሕሊና ወድንግል በሥጋ መሆኗን የሚያስረዳን ነው፡፡ እንኳን ለእናታችን ጽዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን :: እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከት ያሳትፈን፡፡ የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በእኛ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር አሜን!!