Grace Media/ ሁሉ በጸጋ

Grace Media/ ሁሉ በጸጋ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። ኤፌሶን 2:18

 ! 👉 ዛሬ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ አገልጋዮች ለየት ያለ ምስጢር ያገኙ እየመሰላቸው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ውጭ የሆኑ የፍልስፍና መጻሕፍትን የመንፈሳዊ ትምህርት ምንጭ እያደረጉት ይገኛሉ...
06/18/2026

!
👉 ዛሬ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ አገልጋዮች ለየት ያለ ምስጢር ያገኙ እየመሰላቸው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ውጭ የሆኑ የፍልስፍና መጻሕፍትን የመንፈሳዊ ትምህርት ምንጭ እያደረጉት ይገኛሉ። ለዚህ ትልቅ ማሳያ የሚሆነው፣ ከ161 ዓመታት በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን በአለቃ (በደብተራ) ዘነበ የተጻፈውና እየተባለ የሚጠራው መጽሐፍ ነው።

👆ይህ መጽሐፍ በታሪክና በሥነ-ጽሑፍ ደረጃ የሚኖረው ቦታ እንዳለ ሆኖ፣ በውስጡ የያዛቸው ሃሳቦች ግን ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ፣ የእግዚአብሔርን ቃልና አምላካዊ ማንነት የሚያቃልሉ ፍልስፍናዎች ናቸው። ለምሳሌ በመጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል፦

“እግዚአብሔር ፈሪ ነው፤ እኛ በድለነው ልጁን ልኮ ቀስ ብለህ ተዛምደህ ና ብሎ በልጁ ታረቀን... ሰማይን የሚያህል ሰፊ ሀገር ይዞ አባቱ እዚያ አያበላውም፣ አያጠጣውም፣ አያለብሰውም? ልጁስ ሲቀላውጥ ነውር አይፈራምን?” ይላል።

👆ይህ ንግግር መንፈሳዊ ቅኔና ግጥም ሳይሆን ክርስቶስ ስለ እኛ በምድር ላይ መራቡን፣ መጠማቱንና በመስቀል ላይ የከፈለውን ታላቅ የፍቅር መሥዋዕትነት (ማቴዎስ 25) "ነውርና መቀላወጥ" አድርጎ የሚሳለቅ ስጋዊ ፍልስፍና ነው!

📌ትልቁ አደጋ ግን ይህንን የፌዝና የፍልስፍና ጽሑፍ ዛሬ ያሉ "የወንጌል አገልጋዮች" ነቅሰው በማውጣት፣ እንደ እግዚአብሔር ቃልና እንደ ትልቅ ጥልቅ ጥበብ አድርገው ለትውልዱ ማስተማራቸው ነው። ይህ ፍጹም ስህተትና መንፈሳዊ ውድቀት ነው!

?

📌የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ትምህርቷን፣ ስብከቷንና ራዕይዋን መቅዳት ያለባት ከእውነተኛውና ከሕያው የእግዚአብሔር ቃል፣ ከመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ብርሃን ብቻ ነው።

📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሲያስተምር የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት እየጠቀሰ (ኦሪትንና ነቢያትን) ነበር።

📌ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና የጥንቷ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ምስክርነታቸውንና ስብከታቸውን የገነቡት የቅዱሳት መጻሕፍትን አውድ መሠረት አድርገው ነበር።

!

የዘመኑ አገልጋዮች ግን "የዘመኑን ወጣት ለመማረክ"፣ መጽሐፍ ቅዱስን ዘግተው የደብተራዎችን ተረትና የዓለምን ከንቱ ፍልስፍናዎች ይዘው መድረክ ላይ ይወጣሉ። ወጣቱ ትውልድ የሚፈልገው ግን የሰውን ጥበብ ሳይሆን፣ ሕይወትን የሚለውጠውንና ከኃጢአት የሚያድነውን ንጹሑን የወንጌል እውነት ነው። በሰብአዊ ፍልስፍና የተገነባ አገልግሎት ትውልዱን ለውድቀትና ለክህደት አሳልፎ ይሰጣል። ለዘመኑ ወጣት ክርስቶስን መግበው እንጂ ፍልስፍናና ተረት አትመግበው!

!

እኛ አገልጋዮች ስብከታችንንና ትምህርታችንን መቅዳት ያለብን ከጳውሎስና ከአዲስ ኪዳን ሐዋርያዊ እውነት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ያስጠነቀቀን ማስጠንቀቂያ ዛሬም በቤተክርስቲያናችን ጮሆ ሊሰማ ይገባል፦

“እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለም መጀመሪያ ትምህርት በሰው ጥበብና በከንቱ ማታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።" (ቆላስይስ 2፥8)

:-

ወደ ቃሉ እውነት እንመለስ! የዓለም ፈላስፎች ሐሳብ መድረካችንን አይውረሰው። መድረክ የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ብቻ በስልጣን የሚነገርበት ቅዱስ ስፍራ ነው። ለየት ለማለትና ሰውን ደስ ለማኘት ስንል ከንጹሑ ወንጌል ፈቀቅ የምንል ከሆነ፣ ተጠያቂነታችን በእግዚአብሔር ፊት የበረታ ይሆናል። ለዘመኑ ወጣት የዓለምን ፍልስፍናና ተረት ሳይሆን ክርስቶስን መግበው! እርሱ የሕይወት እንጀራ ነው!
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!

ጸጋዬ ግርማ

 :-  !👉 ሰሞኑን መነጋገሪያ በሆነው “አብ ይጣዳል፣ ወልድ ይፈላል፣ መንፈስ ቅዱስ ይገነፍላል” በሚለው ትምህርት ዙሪያ፣ የትምህርቱን ምንጭና የሰባኪውን ስህተት በተመለከተ ቀደም ሲል መግለ...
06/17/2026

:- !

👉 ሰሞኑን መነጋገሪያ በሆነው “አብ ይጣዳል፣ ወልድ ይፈላል፣ መንፈስ ቅዱስ ይገነፍላል” በሚለው ትምህርት ዙሪያ፣ የትምህርቱን ምንጭና የሰባኪውን ስህተት በተመለከተ ቀደም ሲል መግለጼ ይታወሳል። አሁን ግን ነገሩን ይበልጥ በጥልቀት ስንመረምረው፣ ችግሩ የሰባኪው ቃላትን ማዛባት ብቻ ሳይሆን፣ ከመነሻው የትምህርቱ ምንጭ ራሱ ፍጹም ስህተትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው መሆኑን በግልጽ ማሳየት ያስፈልጋል።

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ያያያዝኳቸውን ምስሎች ለዚህ ማረጋገጫ ይመልከቱ። እውነታው ግን የሚከተለው ነው፦

📌 የትምህርቱ ምንጭና አመጣጥ:-

👆ይህ ትምህርት ዛሬ በድንገት ከመንፈስ ቅዱስ የወረደ አዲስ “መለኮታዊ መገለጥ” (Divine Revelation) ሳይሆን፣ የታሪክ ማኅደር የሚያጋልጠው የሰዎች የቆየ ፍልስፍናዊ ድርሰት ነው።

👉 የዚህ ንግግር (አብ ይጣዳል፣ ወልድ ይፈላል፣ መንፈስ ቅዱስ ይገነፍላል) እውነተኛ ምንጭ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት ታዋቂው የኦርቶዶክስ ሊቅ “ደብተራ ዘነብ” (ከዘነብ ኢትዮጵያዊ) በ1857 ዓ.ም የጻፉት «መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ» የተሰኘው መጽሐፍ ነው (በምስሉ ላይ እንደሚታየው)።

✍️ደብተራ ዘነብ ይህንን መጽሐፍ አዘጋጅተው፣ በራሳቸው እጅ በወረቀት ጽፈው የጨረሱት በ1857 ዓ.ም. ነው። በዚያ ዘመን (በዓፄ ቴዎድሮስ ዘመን) በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ የሕትመት መሣሪያ (ማተሚያ ቤት) ስላልነበረ፣ መጽሐፍት የሚዘጋጁት በእጅ ተጽፈው አንድ ወይም ጥቂት ኮፒ ብቻ ነበር። ስለዚህ መጽሐፉ ተጽፎ ለብዙ ዓመታት የተቀመጠው በዕጅ ጽሑፍ መልክ ነበር።

👆ይህ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1924 ዓ.ም በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ በድጋሚ ደግሞ በ 1946 ዓ.ም በተስፋ ማተሚያ ቤት የታተመ የሰዎች የባህልና የፍልስፍና ሥራ ነው።

👉ደብተራ ዘነብ በመጽሐፋቸው ላይ ይህንን አባባል ሲያስቀምጡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትን ሳይሆን፣ የራሳቸውን ሰዋሰዋዊና ምድራዊ ፍልስፍና ነበር። መለኮታዊውን የሥላሴን ባሕርይ “ከመፍላትና ከመገንፈል” (የምግብ አዘገጃጀት ወይም የቁስ ዑደት በሚመስል) ምድራዊ ዘይቤ ለመግለጽ መሞከራቸው የመጀመሪያውና ትልቁ የስህተት ትምህርት (Theological Error) ነው።

👉እግዚአብሔር በባሕርዩ የማይለወጥ፣ የማይበላሽና ፍጹም መንፈስ እንጂ በቁሳዊ ምሳሌ የሚገለጥ አይደለም። ስለዚህ ደብተራ ዘነብ የተናገሩትም ቢሆን በፍጹም እውነት አይደለም፤ የእርሳቸውም የቆየ ስህተት ነው።

📌የዮናታን አክሊሉ ስህተት:-

ዮናታን አክሊሉ ደግሞ ይህንን የቆየ የፍልስፍና ድርሰት በቀጥታ በመውሰድ፣ ዛሬ ለምዕመናን ከመንፈስ ቅዱስ የወረደ አዲስ “መለኮታዊ መገለጥ” አድርጎ ማስተማሩ ሁለተኛውና የከፋው ስህተት ነው።

👉የእግዚአብሔር ቃል የሕይወትና የእምነት መሠረት በሆነበት የወንጌል አማኞች መድረክ ላይ፣ የሰውን የቆየ የስህተት ድርሰት እንደ ሰማያዊ መገለጥ ማቅረብ ታላቅ ማታለል ነው።

👉 ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የቃላት ጨዋታ ሕዝቡ በደብተራቸው ላይ “ጻፉት” ብሎ ማዘዝ፤ የሰዎችን ልብ ከእግዚአብሔር ቃል አውጥቶ በሰው ፍልስፍና ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ ነው።

👉መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ፍጹም ቅዱስ፣ ኃያልና ሉዓላዊ አድርጎ ይገልጠዋል እንጂ “ይፈላል፣ ይገነፍላል” በሚሉ ምድራዊና ቁሳዊ ሂደቶች በጭራሽ አይገልጠውም። ይህ አገላለጽ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ ያደርጋል።

👉የደብተራ ዘነብ ድርሰትም ሆነ የዮናታን አክሊሉ ስብከት የሰዎችን ጆሮ ለመሳብ የተደረገ የቃላት ድራማ እንጂ ሰዎችን ወደ ንስሐና ወደ ክርስቶስ መስቀል የሚያመጣ የወንጌል እውነት የለውም።

🎯የወንጌል አማኝ ልንሆን የሚገባን የእግዚአብሔር ቃል ተከታዮች እንጂ የሰዎች የፈጠራ ታሪክና የስህተት ድርሰቶች ተከታዮች አይደለንም። ማንኛውንም ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ብቻ እንመርምር!

“ነገር ግን ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤” (1ኛ ተሰሎንቄ 5:21)

ጸጋ ይብዛላችሁ!

ወንድማችሁ ጸጋዬ ግርማ ነኝ

 ?🤔🤔🤔🤔ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የእግዚአብሔርን ማንነትና የምስጢረ ሥላሴን አስተምህሮ ለመግለጽ “አብ ይጣዳል፣ ወልድ ይፈላል፣ መንፈስ ቅዱስ ይገነፍላል” የሚል አባባል እየሰማን ነ...
06/16/2026

?🤔🤔🤔🤔

ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የእግዚአብሔርን ማንነትና የምስጢረ ሥላሴን አስተምህሮ ለመግለጽ “አብ ይጣዳል፣ ወልድ ይፈላል፣ መንፈስ ቅዱስ ይገነፍላል” የሚል አባባል እየሰማን ነው። ይህ አገላለጽ ለአንዳንዶች ጥልቅ ምስጢር ሊመስል ቢችልም፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛን ሲመዘን ግን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚያዋርድና ፍጹም ኑፋቄ የሆነ የሰው ፍልስፍና ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ይህንን የተሳሳተ አስተምህሮ እንዴት ይመዝነዋል?

1. ።

📌ምግብ ሲጣድ፣ ሲፈላና ሲገነፍል የአካላዊና የሙቀት ለውጥ ሒደትን ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሔር የማይለወጥ ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል።

“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤” (ሚልክያስ 3፡6)

“በእርሱ ዘንድ መለወጥ በእርሱም ዘንድ የጥላ መዞር የለም።” (ያዕቆብ 1፡17)

እግዚአብሔርን እንደ ምግብ ማብሰል ሒደት ተለዋዋጭ አድርጎ ማቅረብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

2. ።

📌ይህ አባባል አብን መጀመሪያ፣ ወልድን መካከለኛ፣ መንፈስ ቅዱስን ደግሞ መጨረሻ ላይ የመጣ የኃይል መግለጫ አድርጎ በማቅረብ “የባሕርይ መበላለጥን” ያመጣል። ነገር ግን ወንጌል የሚያስተምረው ሦስቱም አካላት (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) እኩል፣ ዘላለማዊና መጀመሪያ የሌላቸው መሆናቸውን ነው።

ወልድ (ኢየሱስ) መጀመሪያ የሌለው አምላክ ነው፦ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ... ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” (ዮሐንስ 1፡1)

መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ አምላክ ነው፦ “በዘላለም መንፈስ አማካኝነት...” (ዕብራውያን 9፡14)

3.

📌እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐንስ 4፡24)። እርሱን በምድራዊ ቁስና በኩሽና ሒደት መስሎ ለመግለጽ መሞከር ክብሩን ዝቅ ማድረግ ነው። ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
“እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተካክሉታላችሁ?” (ኢሳይያስ 40፡18)

#ማሳሰቢያ:-
📌ማንኛውንም ትምህርት የምንመዝንበት ብቸኛውና የመጨረሻው ባለሥልጣን የእግዚአብሔር ቃል (Sola Scriptura) ብቻ ነው። በጆሮአችን ስላማረ ወይም “ጥልቅ ምስጢር” ስለመሰለን ብቻ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተደገፈን ፍልስፍና አንቀበልም።

📌እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ—አንድ አምላክ በሦስት አካላት፤ ያለ መበላለጥ፣ ያለ መቀዳደም፣ በአንድነትና በእኩልነት ለዘላለም የሚኖር አምላክ ነው።
ከሰው የፈጠራ ፍልስፍና ወጥተን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን በገለጠበት እውነት ላይ እንቁም!

ጸጋዬ ግርማ

#መጽሐፍቅዱስ #ሥላሴ #የእግዚአብሔርቃል #እምነት #ኦርቶዶክስ #ክርስቲያን #ጴንጤ #መዝሙር #ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #እግዚአብሔር #ወንጌል

በሃይማኖት ሽፋን ሰዎችን ከሕክምናና ከመድኃኒት በማራቅ በሰው ሕይወት ላይ የምትቀልዱ የዘመኑ “ነቢያት” ሆይ፤ ይህንን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 በጥንቃቄ አንብቡና ተጠንቀቁ! 📌...
06/13/2026

በሃይማኖት ሽፋን ሰዎችን ከሕክምናና ከመድኃኒት በማራቅ በሰው ሕይወት ላይ የምትቀልዱ የዘመኑ “ነቢያት” ሆይ፤ ይህንን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 በጥንቃቄ አንብቡና ተጠንቀቁ!

📌መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ያላዘዘውን በስሙ የሚናገርን የሐሰት ነቢይ (ዘዳግም 18፥22:- “ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆንና ባይፈጸም፥ ያ ቃል እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በዕብሪቱ ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው”) በማለት እግዚአብሔር ያላዘዘውን በስሙ የሚናገርን የሐሰት ነቢይ በጥብቅ እንደሚኮንንና እንደማይፈራው ሁሉ፣ የምድርም ሕግ በሃይማኖት ስም የሰውን ሕይወት ለአደጋ መጣልን “በቸልተኝነት ሰውን መግደል” በሚል ወንጀል በቀጥታ ይጠይቃል፤

📌 በዚህም መሠረት በኢትዮጲያ ሕግ፤ በአንቀጽ 543 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ማንኛውም ሰው በቸልተኝነት ለአንድ ሰው ሞት ምክንያት ከሆነ እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራትና መቀጮ እንደሚቀጣ ሲደነግግ፣ በንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደግሞ ድርጊቱ ሊያስከትል የሚችለውን አደገኛ ውጤት እያወቁ በዕብሪት ከሆነ፤ ማለትም አንድ በሽተኛ መድኃኒቱን ካቆመ ወይም የመተንፈሻ መሣሪያውን ከነቀለ ሊሞት እንደሚችል እያወቁ “ተፈውሰሃል፥ ጣለው” በማለት ለሞት ምክንያት መሆን ቅጣቱን ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ቀላል እስራትና መቀጮ እንደሚያደርሰው ያስቀምጣል፥ ይባስ ብሎም በንዑስ አንቀጽ 3 ላይ ድርጊቱ ሊያስከትል የሚችለውን ከባድ አደጋ አስቀድሞ ማወቅ ሲገባው ሳይገነዘብ ቀርቶ ለተፈጸመ ጥፋት ቅጣቱ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚሆን በግልጽ ይደነግጋል።

👉 ከምድር ሕግ ባሻገር እግዚአብሔርም ቢሆን በኤርምያስ 6፥14 ላይ “የሕዝቤን ስብራት ሰላም ሳይሆን ሰላም ሰላም እያሉ በጥቂቱ ይፈውሳሉ” እንዳለው፣ ያልዳነን ሰው በሐሰት “ተፈውሰሃል” እያሉ የሐሰት ተስፋ መስጠትንና ሰውን ለሞት መዳረግን በጥብቅ ያወግዛል። በአዲስ ኪዳንም የትንቢት ዓላማ ሰውን ማነጽ፣ መምከርና ማጽናናት እንጂ (1 ቆሮንቶስ 14፥3) መሣሪያ አስነቅሎ መግደል አይደለምና ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 7፥15 ላይ “በውስጣቸው ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” እንዳለ፣ ፍሬያቸው የሰው ሕይወት ማጥፋትና “አይገደኝም” (I don't care) ማለት የሆኑ እግዚአብሔር የማያውቃቸውና ሀሰተኞች ናቸው።

📌 ስለዚህ ሕዝቡ በፈቃዱ መጣ እያሉ በሰው ነፍስ መነገድ በሕግም በእግዚአብሔርም ፊት ከተጠያቂነት በፍጹም አያምልጥም፤ ጠላቶች አይደሉምና እግዚአብሔር ባልሰጣችሁ የውሸት ትንቢት ሰዎችን ከመድኃኒት እያራቃችሁ ለሞት የምትዳርጉ ሁሉ፣ ከሰማዩ የእግዚአብሔር ፍርድ በፊት የምድርም ሕግና ወኅኒ ቤት ከፊታችሁ እንደሚጠብቃችሁ እወቁና ከዚህ አደገኛ ዕብሪታችሁ እንድትመለሱ ወንድማዊ ምክሬ ነው!

ወንድማችሁ ጸጋዬ ግርማ

 #ምሽጎች (STRONGHOLDS)   በአማኝ አእምሮ ውስጥ የሚገነቡ የሃይማኖት ውሸቶች የእግዚአብሔርን እውነተኛ ባሕርይ እንዳናይ የሚከለክሉ ትላልቅ ግንቦች ናቸው። ጠላት እነዚህን ምሽጎች የ...
06/12/2026

#ምሽጎች (STRONGHOLDS)

በአማኝ አእምሮ ውስጥ የሚገነቡ የሃይማኖት ውሸቶች የእግዚአብሔርን እውነተኛ ባሕርይ እንዳናይ የሚከለክሉ ትላልቅ ግንቦች ናቸው። ጠላት እነዚህን ምሽጎች የሚገነባው፣ እኛ ሁልጊዜ በራሳችን ጥረትና ሥነ-ሥርዓት ላይ እንድንደገፍ ለማድረግ ነው።

ቆላስይስ 2:20-22 (NKJV) "ከዓለማዊ መጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥... አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ለሰው ትእዛዝና ትምህርት እንደ ዓለም የምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ?"

የሃይማኖት ምሽግ ምልክቶች፦
እግዚአብሔርን በፍርሃትና በኩነኔ መመልከት። ደኅንነትንና በረከትን በራስ ሥራ ለመግዛት መጣር። በክርስቶስ በተጠናቀቀው ሥራ ላይ ሙሉ ዕረፍት ማጣት።
እነዚህን ምሽጎች ለማፍረስ፣ በመስቀል ላይ የተከናወነውን የጸጋ ወንጌል ያለ ምንም ቅልቅል በአእምሯችን ውስጥ መቅረጽ አለብን

(PULLING DOWN STRONGHOLDS)

በአእምሯችን ውስጥ የተገነቡትን ምሽጎች ማፍረስ ማለት እነዚህን ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የማይስማሙ የአስተሳሰብ መዋቅሮችን በንቃት ማፍረስ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ "እናፈርሳለን" (pulling down) የሚለውን ቃል ሲጠቀም፣ ይህ በአማኙ በኩል የሚደረግ ንቁ እና ቆራጥ ተግባር መሆኑን ያሳያል።

እነዚህ ምሽጎች የሚፈርሱት በሰው ምኞት ወይም በሥጋዊ ጥረት ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ በሆነው በቃሉ እውነት ኃይል ነው።

የመጀመሪያው እርምጃ በአእምሯችን ውስጥ ያሉትን የተሳሳቱ እምነቶች እና የሃይማኖት ውሸቶች መለየት ነው።

በዮሐንስ 8:32 ላይ እንደተጻፈው፦ "እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።" ነጻ የሚያወጣን የምናውቀውና በአእምሯችን የምንቀበለው እውነት ብቻ ነው።

(“መለኮታዊ አስተሳሰብ” በሚል አርስት የተፃፈው የእንግሊዘኛ መፅሐፍ ወደ አማርኛ እየተተረጎመ ነው። ይህ ፅሁፍ ከመፅሐፉ ላይ የተወሰደ የቅምሻ አሳብ ነው)

06/10/2026
06/10/2026

የኃይማኖት ሱቆች ተዘግተዋል። ከእነርሱ ለመሸመት አትሂዱ! The religion shop has been closed.
Amazing teaching!

06/08/2026

የአቤል ደም “ፍረድልኝ”ሲል፣ የክርስቶስ ደም ግን “ማርልኝ” ይላል! እኛ ዛሬ የዳነው በዚህ በተሻለው ደም ነው። ዕብ 12:24

በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረውን ሰው ማረድ ፈጣሪን ማምለክ ሳይሆን የሰይጣን ተግባር ነው!"ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጡር ነው፡ መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት 1፥27 ላይ...
06/07/2026

በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረውን ሰው ማረድ ፈጣሪን ማምለክ ሳይሆን የሰይጣን ተግባር ነው!

"ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጡር ነው፡ መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት 1፥27 ላይ "እግዚአብሔርም ሰውን በአምሳሉ ፈጠረው" ይላል። ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ነፍስ ማጥፋት የፈጠረውን አምላክ መዳፈር ነው።

በአርሲ ምድር በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ የጭካኔ ግድያ፣ ማረድና ማሳደድ ሰብአዊነትን ብቻ ሳይሆን ፈጣሪንና ሃይማኖትንም የሚሳደብ ተግባር ነው።

ፈጣሪን እናስደስታለን እያሉ ሰውን ማረድ ከሰይጣናዊ ስውር ተልዕኮ ውጪ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም።
ሃይማኖት የሰላም እንጂ የደም መፍሰሻ አይደለም።

የእስልምና እምነት ስሙ ራሱ "ሰላም" (Salam) ከሚለው ስርወ-ቃል የመነጨ ሆኖ ሳለ፣ የእምነቱን ስም መጋረጃ በማድረግ ንጹሐንን ማረድ የሃይማኖቱን አስተምህሮ መጣስና ፅንፈኝነት ነው።

የቃየል መንፈስ ይወገዝ፡ "ከክፉው የነበረ ወንድሙንም የገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።" (1ኛ ዮሐንስ 3፥12)። ዛሬም ንጹሐንን የሚያርዱ ፅንፈኞች የቃየልን የጭካኔ መንገድ እየተከተሉ ነው።

ፈጣሪ ፍርድንና ፍትሕን በምድራችን ላይ ያውርድ። ለተገደሉት ወገኖቻችን ሰማያዊ ዕረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተከታዮች መጽናናትን ይስጥ።




#ኦርቶዶክስ #አርስ #ኢትዮጵያ #ክርስቲያን #ሙስሊም #ቁራን #መጽሐፍቅዱስ

06/06/2026

“በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።” ሮሜ ሰዎች 5:2
📌ጸጋ ለማግኘት የምንጥረው ወይም የምንታገለው ነገር ሳይሆን፣ በክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የገባንበትና ጸንተን የቆምንበት መሠረታችን ነው!

Address

Vancouver, BC

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grace Media/ ሁሉ በጸጋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share