Grace Media/የወንጌል እውነት

Grace Media/የወንጌል እውነት በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። ኤፌሶን 2:18

የቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እየወሰደች ያለችው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እርምጃ እጅግ የሚያበረታታና ለሌሎችም መልካም አርአያ የሚሆን ነው! 🙏
09/04/2026

የቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እየወሰደች ያለችው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እርምጃ እጅግ የሚያበረታታና ለሌሎችም መልካም አርአያ የሚሆን ነው! 🙏

08/26/2026

እኛ በተፈጥሮአችን የእግዚአብሔር ጠላቶችና የቁጣ ልጆች ነበርን (ኤፌሶን 2:3)። ነገር ግን በኢየሱስ ደም ተዋጅተን ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ ገባን፤ የእግዚአብሔርም ወራሾች የመሆን ሕጋዊ መብትና ሥልጣን ተሰጠን። ሮሜ 8:15

08/26/2026

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው በባህርዩ፣ በመለኮቱና ከእግዚአብሔር አባት ጋር ባለው ዘላላማዊ አንድነት ነው። እኛ ግን በጸጋና በክርስቶስ በኩል ነው ልጅ የሆንነው።

08/26/2026

እኛ ጉዲፈቻ ብቻ ነን ብሎ የዳግም ልደቱን ህያው ተፈጥሮ መካድ ወይም እኛ የእግዚአብሔር የባህርይ ዘሮች ነን ብሎ የፈጣሪና የፍጡርን ድንበር ማፍረስ ሁለቱም ስህተት ናቸው።

08/15/2026

ቤተ ክርስቲያን (Ekklesia-ἐκκλησία) የሚለው ቃል ትርጉም «ለአንድ ዓላማ ተጠርቶ የወጣ ጉባኤ» ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን የተባሉት ዳግመኛ የተወለዱትና የክርስቶስ አካል የሆኑት የወንጌል አማኞች እንጂ ሕንፃው ወይም አዳራሹ አይደለም።

በዘመናችን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት፣ የ15 ዓመት፣ የ20 ዓመት፣ 40ኛ ዓመት ወይም 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል” እያሉ ማከበር የተለመደ አሰራር ሆኗል። ነገር ግን ይህ ልምምድ በአዲስ...
08/15/2026

በዘመናችን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት፣ የ15 ዓመት፣ የ20 ዓመት፣ 40ኛ ዓመት ወይም 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል” እያሉ ማከበር የተለመደ አሰራር ሆኗል። ነገር ግን ይህ ልምምድ በአዲስ ኪዳን እውነት ሲመዘን ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው እና የክርስቶስን አካል እንደ ግል ድርጅት የመቁጠር ስህተት ነው።

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ምስረታና እድገት ምን ያስተምራል? የሚከተሉትን ጠንካራ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እንመልከት፦



ኢየሱስ ክርስቶስ "ቤተ ክርስቲያኔን እሰራለሁ" አለ እንጂ "የእገሌን ቤተ ክርስቲያን ትሰራላችሁ" አላለም (ማቴዎስ 16:18)። ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተዋጀች ሕያው አካል ነች (ሐዋርያት ሥራ 20:28)። አንድ ግለሰብ ወይም ፓስተር ህንፃ ስለተከራየ ወይም የራሱን ስብሰባ ስለጀመረ "የቤተ ክርስቲያኔ የምስረታ በዓል" ማለቱ፣ የክርስቶስ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን እንደ ግል ኩባንያ ወይም ንግድ ድርጅት የመቁጠር አደገኛ አካሄድ ነው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስም ሆኑ ሌሎች ሐዋርያት የተከሏቸውን አብያተ ክርስቲያናት (የኤፌሶን፣ የቆሮንቶስ፣ የገላትያ ወዘተ) ዓመታዊ የምስረታ በዓል አላከበሩም።

የሐዋርያት ትኩረት የተጠናቀቀውን የክርስቶስን የጸጋ ወንጌል ማወጅ እንጂ፣ የአገልግሎታቸውን ዘመን ወይም የተቋማቸውን እድሜ ማክበር አልነበረም። ይህ አሰራር ከዓለማዊ ባህል ኮፒ ተደርጎ ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ነው።

አብዛኞቹ የአኒቨርሰሪ ፕሮግራሞች ትኩረታቸው ወደ ፓስተሩ ስኬት፣ ወደ ህንፃውና ወደ ድርጅቱ እድገት የሚያደሉ ናቸው። ነገር ግን የወንጌል እውነት ማዕከል ክርስቶስ ብቻ ነው።

"ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" (ገላትያ 6:14)። የሰውን አገልግሎትና የተቋምን ዘመን ማክበር ትኩረትን ከክርስቶስ መስቀል ወደ ሰው ስራ ያዞራል።



መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጻት እንደ "የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን" (1ኛ ጢሞቴዎስ 3:15) እና እንደ "የክርስቶስ አካል" (1ኛ ቆሮንቶስ 12:27) አድርጎ ነው።
የምስረታ በዓል የሚያስፈልገው ላለፈ ታሪክ ወይም ለሰዎች ድርጅት ነው። ሕያው የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በየእለቱ በክርስቶስ ሕይወት የምትኖር እንጂ በዓመት አንድ ቀን የቀን መቁጠሪያ እየጠበቀች የምታከብር ተቋም አይደለችም።

📌ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እና በጴንጤቆስጤ ቀን በመንፈስ ቅዱስ ወረደበት ቅጽበት ነው! ግለሰቦች የራሳቸውን ድርጅታዊ አኒቨርሰሪ ማክበራቸው አዲስ ኪዳናዊ መሠረት የለውም። በክርስቶስ ደም የተዋጀች ቤተ ክርስቲያን በየእለቱ ክርስቶስን ታከብራለች፣ ታስባለች፣ ትሰብካለች እንጂ እንደ ባልና ሚስት Anniversary እያለች ማክበር ይለባትም።

ጸጋ ይብዛላችሁ!

ጸጋዬ ግርማ

08/15/2026

ቤተ ክርስቲያን ሕያው አካል እንጂ የታሪክ መታሰቢያ አይደለችም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ እንጂ የሰው አይደለችም።

08/11/2026

Address

Vancouver, BC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grace Media/የወንጌል እውነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share