Hamere Noah Kitchener Kidanemhret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

Hamere Noah Kitchener Kidanemhret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church THE CHURCH OUT REACHES TO MEMBERS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX AND OTHER COMMUNITIES WITH TEACHING OF SPIRITUAL AND SOCIAL BEING.

 #ሰኔ 12/2018                 #የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ                       ይሰፍራል ያድናቸዉማል መዝ.33፥7-9  🍁በስመ  #አብ _ወወልድ...
06/19/2026

#ሰኔ 12/2018


#የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ
ይሰፍራል ያድናቸዉማል መዝ.33፥7-9

🍁በስመ #አብ _ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በፆምና በፀሎት ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #አፎምያን ከሰይጣን እጅ ላዳነበት #ባህራንን ለተራዳበት ዓመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

🍁 ይህችም ሴት #እግዚአብሔርን የሚፈራ የአንድ ሰው ሚስት ነበረች ባሏ አስተራኒቆስ በታመመ ጊዜ እያዘነችና እያለቀሰች እንዲህ አለችው ጌታዬ አንድ ነገር ልንገርህ እስኪ ስማኝ ሴት ባሏ የሞተ እንደሆነ ብቸኛ ባይታወር ጦም አዳሪ እንደምትሆን እንጀራዋንም በብዙ ዕንባና ሰቀቀን እንደምትመገብ አንተ ታውቃለህ አንተ ብትሞትና ብትለየኝ ከኀዘኔ የሚያረጋጋኝ ልጅ አባት እናት የለኝም

🍁 አሁንም አንተ ሳለህ የመላእክት አለቃ ሥዕል እንድታሰራልኝ እሻለሁ በመዓልትም በሌሊትም ከሰይጣን ጠላትነት ይጠብቀኝ ዘንድ እኔ በቤቴ ውስጥ አኑሬ እማፀንበታለሁ አስተራኒቆስም አስሎ ሰጣት ባሏም ከሞተ በኋላ ቅድስት አፎምያ ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር

🍁 በዚህ ሰይጣን ቀናባት በመነኩሴ ተመስሎ ሊያስታት ሞከረ ስዕል አሳፍራ መለሰችው ከ 3 ወራት በኋላ ሰኔ 12 ቀን ዳግመኛ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ ሊፈትናት መጣ ሚካኤል ከሆንክ መስቀልህ የት አለ አለችው ከዚህ በኋላ አፉን ከፍቶ አይኑን አጉረጥርጦ አንገቷን አነቃት

🍁 ድረስልኝ ብላ ተጣራች ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወረደ በበትረ መስቀሉም መታው ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ ስዕልህ ባለበት ስምህ በተጠራበት ድርሳንህ በሚነበብበት ፈፅሞ አልደርስም ብሎ ማለ ተገዘተ ሸሸም ከዚህ በኋላ ወዳጄ አፎምያ ባንቺ ደስ አለኝ ዋጋሽ በሰማይ ታላቅ ነው ብሎ ባርኳት አርጓል

🍁እንዲሁም በዚህ እለት ባህራንን የተራዳበት የሞቱን ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረበት የተአምር በዐል ነዉ እንኳን አደረሰን

🍁ከቀድሞ ጀምሮ ቂም የሌለበት ምህረትን የሚለምን እሩሩህ ልመናው ከሲኦል ረግረግ ያድነን ከርጉም ተኩላ አፍም ይሰውረን በከንቱ እንዳንጠፋ ከክፉ የሰይጣን ወጥመድም ያድነን ከሰራዊቱ ሁሉ ጋር በየቀኑ ይታደገን

🍁 ረድኤት በረከታቸዉ ከኛ ጋር ይሁን ጥበቃዉ አይለየን የአባቶቻችን ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን"አሜን"

ሰኔ 10/2018   👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችን   በመስቀሉ ክብር ለምናመሰግንበት   ለተገኘበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን  አደረሰን 👉እውራንን የሚ...
06/17/2026

ሰኔ 10/2018


👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችን በመስቀሉ ክብር ለምናመሰግንበት ለተገኘበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውራንን የሚያበራው ድውያንን የሚፈውሰው ሰላመ #እግዚአብሔርን ያገኘንበት የድህነታችን አርማ ሀይላችን የምንመካበት የምንድንበት ቅዱስ ነው

👉የድህነታችን አርማ የሆነውን ቅዱስ አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ቀበሩት ለዘመናት የቆሻሻ ክምር በመጣል መስቀሉ እዲሰወር አደረጉ

👉በ 320 ዓ.ም የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ልጇ ቆስጠንጢኖስ ከአረማዊ እምነት ወደ ክርስትና እንዲመለስ ስለት ተሳለች በስለቷ መሰረት ልጇ ወደ ክርስትና አምነት ከተመለሰ ለማግኘት በተሳለችው ስለት መሰረት መስከረም 16 ደመራ ደምራ እጣን በውስጡ ጨምራ አበራች

👉በዚህም ወቅት ጢሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ ወደ ምድር ሰግዶ በዘመኑ ከነበሩት ብዙ የቆሻሻ ክምር ተራራዎች የጌታችን ወዳለበት ተራራ አመለከተ

👉 መስከረም 17 ቁፋሮውን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን ቅዱስ እፀ መስቀሉ ተገኘ።

👉መድኃኒታችን ከመስቀሉ መታሰቢያ ክብረ በአል በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን የቅዱሳን ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️

       🍁 በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን   🍁እንኳን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት  #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን    🍁  ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለ...
06/14/2026



🍁 በስመ አሐዱ አምላክ አሜን
🍁እንኳን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

🍁 ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው

🍁 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው

🍁 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ.1፥2 ምሳ.30፥4

🍁 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ.2፥7

🍁 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ

🍁 #ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

🍁 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

🍁 ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።

🍁 ስሞች ትርጉም

🍁 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርፅ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረፀ ነው።

🍁 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ.2፥7

🍁 ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው ኢዮ.26፥13

🍁አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በረድኤት በበረከት ይጎብኙልን

🍁ከሶስቱ አካል አንዱ በሞቱ ሞታችንን የሻረልን በተቀደሰችዉ #ትንሣኤው ላከበረን ምስጋና እና ክብር ይገባዋል "አሜን"

​አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ በረከታቸው ይደርብን፤
#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጸሎት

 #ሰኔ6     🍁የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳሌ 10: 7  🍁እንኳን ለቅድስት አርሴማ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን፡፡   🍁ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ቀን በዕለተ ሐሙስ ተወለደች...
06/13/2026

#ሰኔ6

🍁የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳሌ 10: 7

🍁እንኳን ለቅድስት አርሴማ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

🍁ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ቀን በዕለተ ሐሙስ ተወለደች፡፡

🍁አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትዮስ ይባላሉ፡፡ አባቷ የቤተመቅደስ አገልጋይ ካህን ነበር፡፡

🍁ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ መልኳ ያማረና እጅግ ውብ ስለነበረች ድርጣድስ የተባለ ንጉስ በውበቷ ተማርኮ ተመኛት ለጣኦት እንድትሰግድ አስፈራራት፡፡ እርሷ ግን ለእግዚአብሔር እንጂ በሰው እጅ ለተሰራ ጣኦት አልሰግድም አለችው፡፡

🍁ንጉስ ድርጣድስ በንዴት መከራና ስቃይ አጸናባት እስር ቤትም አስገባት፡፡ ግንቦት 11ቀን እስር ቤት ገባች፡፡ በእስር ቤተ ሳለችም የህይወት መጠጥ የያዘ ጽዋ ከሰማይ ወረዶላታል፡፡ መስከረም 29 ቀን አንገቷ ተቆርጣ ሰማዕትነትን ተቀብላለች፡፡

🍁ሰላም ለመቃብርኪ
ከሰማዕታ ጋራ ካረፍሽበት አርመንያ ቦታ ለመቃብርሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ በአርአያና በምሳሌ ከተናገርኩት ክብርሽ የተነሳ የሽንገላ እጅ ያለዳሰሰሽ የመነሳት ዕቃ አርሴማ ሆይ ከከንፈርሽ ምስጋና ይጥገብ፡፡

🍁ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ
በፈጣሪ ቃል ለተመሰገነ ለሥጋሽ መፍለስ ሰላምታ ይገባል፡፡ የዚህ ዓለም ኑሮንም ላልፈለገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ብፅዕት አርሴማ ሆይ ችግርን እንዳላይ ከበረከት ዕቃሽ መግቢያ ማረስን አልችልምና ጥቂት በረከት ትሰጭኝ ዘንድ እለምንሻለን፡፡

መልክዐ አርሴማ

 #ሰኔ 5/2018    🍁በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን     🍁ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው ...
06/12/2026

#ሰኔ 5/2018

🍁በስመ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

🍁ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማፀን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

🍁በዚህ መሠረት አባታችን መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል

🍁በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

🍁መላእክት ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን

🍁በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ ከኛ ጋር ይሁን በሞቱ ላዳነን በትንሣኤዉ ላከበረን ምስጋና እና ክብር ይሁንልን "አሜን"

 🍁ቅዱስ ዮሐንስ ለጌታውና ለፈጣሪው ለመድኃኔዓለም ክርስቶስ ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ...
06/11/2026



🍁ቅዱስ ዮሐንስ ለጌታውና ለፈጣሪው ለመድኃኔዓለም ክርስቶስ ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል፡፡” ብሎ ሳይፈራ ከእግረ መስቀሉ በመዋል በጽኑ እምነት አስመስክሮአል፡፡

🍁በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ከእመቤታችን ጋር ከእግረ መስቀሉ ባየው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ፣ ያጽናናሽ”፤ ብሏታል፡፡

🍁ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስም “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎታል፡፡ ዩሐ. 19፥26፡፡

🍁ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጌታው ቃል እመቤታችንን ወደ ቤቱ ይዟት ስለሄደ እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ አስራ አምስት አመት ተቀምጣለች፡፡

🍁ከዚህም ኃይለ ቃል የምንማረው እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ እንደኖረች ሁሉ በልበ ምእመናንም አድራ በሃይማኖት የምታጸና፣ ምግባረ ሃይማኖትን፣ ሕገ ትሩፋትን የምታሰራ፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ድኀነተ ስጋን ድኀነተ ነፍስን፣ በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን የምታሰጠን መሆንዋን ነው፡፡

🍁ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

 #ሰኔ 3/2018  👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን   ‹‹በዓታ ማርያም›› እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበትን ዕለት የምናስብበት ነው፡፡🍁ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት...
06/10/2026

#ሰኔ 3/2018


👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን

‹‹በዓታ ማርያም›› እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበትን ዕለት የምናስብበት ነው፡፡

🍁ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ስእለታቸውን አስበው ድንግል ማርያምን በ3 ዓመት ዕድሜዋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዷት።

🍁የአምላክ እናት ከእናት ከአባቷ ቤት ተለይታ እግዚአብሔር ወደመረጠላት ሥፍራ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡

🍁ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡

🍁የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከትና ምልጃ አይለየን🙏

"ሰላም ለልደትኪ ኦ እግዝዕትዬ ማርያም ፤                                       እስመ ኮነ ልደትኪ ምክንያተ ድሂን ለዓለም "እንኳን የዓለሙን መድኃኒት ለወለደችልን ፍፅ...
06/08/2026

"ሰላም ለልደትኪ ኦ እግዝዕትዬ ማርያም ፤ እስመ ኮነ ልደትኪ ምክንያተ ድሂን ለዓለም "
እንኳን የዓለሙን መድኃኒት ለወለደችልን ፍፅምት እመቤት ወርሃዊ የልደት መታሰቢያ አደረሳችሁ

 #ግንቦት 30/2018            "እዉነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል     የሚበልጥ አልተነሳም ማቴ.11፥11"👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   በ...
06/07/2026

#ግንቦት 30/2018


"እዉነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
የሚበልጥ አልተነሳም ማቴ.11፥11"

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉የጌታችን ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው

👉 ነብይ ካህን መምህር ሐዋርያ ፃድቅ አጥማቂ ሰማእት ነው ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል

👉 ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ ክብር የተናገረው

👉ትንቢት የተነገረለት ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን የቅዱሳን ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን

👉 አምላካችን መድኃኒታችን ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የተባረከ ይሁንልን "አሜን" ✝️

 #ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶ...
06/03/2026

#ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።

የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።

የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

©️የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

Address

1677 Snyder's Road E, Petersburg
Kitchener, ON
N0B2H0

Opening Hours

Monday 7am - 11am
Tuesday 7am - 11am
Wednesday 7am - 11am
Thursday 7am - 11am
Friday 7am - 11am
Saturday 6am - 12am
Sunday 5am - 1pm

Telephone

+12266000198

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hamere Noah Kitchener Kidanemhret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share